Wednesday, December 23, 2020

'ህገ መንግስት'?

 

'ህገ መንግስት'?


ያኔ 

መሰረት ሲበጃጅ

ላገር እንዳዲስ ቤት፣

ዳቦ ስም ሲወጣ፣

ለዘመን ህልም ማሸት፤

ምን አሰበን ነበር

ያልነው "ተስማምተናል፣"

ነገድነት ይንገስ

ሰውነት በቅቶናል!

 

አይደለም ወይ ቃሉ

የሰነዱ አንድምታ

ሃገር ሰው አልባ ትሁን

ነገድ ብቻ እውነቷ?

 

ዛሬ 

ታድያ  ደርሰን

"አቤት" "ዋይ" ምንለው፣

በነገድ ፍርድ ቤት

ሰው መቼ ደም አለው?

በቋንቋስ ምህዋር ውስጥ፣

እልቂት መች ፍች አለው?  


ነገ 

ሰነዱን ቁመት፤ ወርድና፤ ጥጋጥግ

በልተን፤ሰንጥቀን፤ህመሙን ሳንፈልግ

ሰውነትን ሳንዋጅ፣ ሰውን ሳንደነግግ

እልቂት ብንረግም በደም ብንበረግግ፣

መሆናችህ አይደል በሃሳዊ ብግነት

ላራጅ ለገፋፊ ቢላ ሚያፈላልግ?

....................................................................

=ኢትዮጲያ ህገ መንግስት መስረታዊ ተፋልሶዎች በፈጠሩት  መድልዎ ምክንያት በየግዜው ህይወታችውን ለሚያጡ ዜጎች።  

No comments: