Friday, April 24, 2015

ህዝቡም አለ!

ትላንት፡

ህዝቡለፋቨስቱ ግራዚኒ ሃውልት በሀገረ ጣልያን መሰራቱ ለገደላቸው ኢትዮጵያውንና ለሀገራችን ክብረነክ ነው አለ፡፡ ብሎም ሰልፍ ወጣ፡፡ ወጥቶም በሃገሩ ፖሊስ -በራሱ ዘ.ጎች- ተደበደበ፡፡ መንግስትም አለ፡መደብደባቸው ትክክል ነው፤፤የሰልፍ ፊቃድ የላቸውም፡፡

 አሁን፡-
ህዝቡ በደቡብ አፍሪካ ከዛም በየመን ከዛም በሊቢያ ዚጎች ዘግናኝ ሞት መጋታቸው ለኢትዮጵያ ክብረነክ ለዚጎችምአንገብጋቢ ነው አለ፡-፡፡ ብሎም ሰልፍ ወጣ፡፡ ወጥቶም በሃገሩ ፖሊስ-በራሱ ዘ.ጎች- ተደበደበ፡

መንግስትም አለ፡(የሰልፍ ፊቃድ የላቸውም አንዳይባል ራሱ መንግስት ነው ጠሪው!) -ሊላ ምክንያት- ፡ ሰልፈኞች መንግስትን -በራሱ ሰልፍ- ላይ ለምን ተቃወሙ!!

ህዝቡምአለ
በመብት-በዚግነት ክብር-በነጣነት-በሁለንተናዊ ልማት ጉዳይ የራሳችንን መንግስት ካልሞገትን ሲልም ካልተቃወምን ታድያ ማንን! ነው ወይስ መንግስት የህዝብን ምሪት የመሰማቱንም ስራ ለቻይና ኮንትራት ሰጥቶታል!!!





No comments: